አዲስ አበባ ከተማ ምንም እንኳን ከሌሎች የአሪካ ከተሞች ጋር ስትነጻጸር ዕድሜዋ አጭር ቢሆንም የአፈሪካ መዲና ብቻ ሳትሆን ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ መሆን ችላለች፡፡ የከተማቱ ዋና ከተመ መሆን ያልተዋተላቸው አንዳንድ ሀገራት በየጊዜው ያልተሟላውን መሰረተ ልማት፣የተንቀራፈፈውን የአገልግሎት ዘርፍ እነቀሱ በማውጣት በየጊዜው ተቀናቃኝነታቸውን ማሳየታቸው አልቀረም፡፡ ክርክሩን መሪዎቻችን ማሸነፍ የቻሉት የሚነሳው የመከራከሪያ ነትብ ስህተት በመሆኑ አልም ከሌሎች የተሻለች መሆን ስለቻለች አይደለም፡፡ ይልቁኑ አፍሪካውያን ለነጻነታቸው ያደርጉት የነበረውን ትግል ማገዝ በመቻልዋና ለአፍሪካ አንድነት መቋቋም በሰጠችው ድጋፍ ሳቢያ መሆኑን ደጋግመን አይተናል፡፡ይህ ክርክር እስከወዲያኛው የተዘጋ አይደለም በየጊዜው የሚነሳ ብቻ ሳይሆን እንደቀደመው ጊዜ ቀደም ሲል የተዋለ ውለታ እየተጠቀሰ መሻገር ፍጹም አይቻልም፤የጎደለውን ለይቶ ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡ 10ኛው መሪ ፕላን ከተማቱ በ2032 ተመራች ዓለም አቀፍ ከተማ የማድረግ ራዕይ ሰንቋል፡፡ይህን ራዕይ ዕውን ማድረግ የሚያስችሉ ግቦችና ተግባራት በየጥናት ርዕሱ በከተማ ልማት ፕላን መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎች ያጠኗቸውን ፈንጠቂ ትናቶች መሰረት ተለይተው በስልታዊ ፕላኑ ተካትተው ተግባራዊ መሆን ጀምረዋል፡፡ የከተማ ፕላን ጉዳይ ስፓሺያል ጉዳ ብቻ አይደለም፤ ከሰው ልጅ አስተሳሰብ ጋር ቁርኝት ያላቸው ከመሬትና ከገጸ ምድር ጉዳዮች በላ የሆኑ እጅግ ጠናና ጉዳዮችን የሚይዝ ነው፡፡