ከተሜነት

1.መግቢያ አዲስ አበባ ከተማ ምንም እንኳን ከሌሎች የአሪካ ከተሞች ጋር ስትነጻጸር ዕድሜዋ አጭር ቢሆንም የአፈሪካ መዲና ብቻ ሳትሆን ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ መሆን ችላለች፡፡ የከተማቱ ዋና ከተመ መሆን ያልተዋተላቸው አንዳንድ ሀገራት በየጊዜው ያልተሟላውን መሰረተ ልማት፣የተንቀራፈፈውን የአገልግሎት ዘርፍ እነቀሱ በማውጣት በየጊዜው ተቀናቃኝነታቸውን ማሳየታቸው አልቀረም፡፡ ክርክሩን መሪዎቻችን ማሸነፍ የቻሉት የሚነሳው የመከራከሪያ ነትብ ስህተት በመሆኑ አልም ከሌሎች የተሻለች መሆን ስለቻለች አይደለም፡፡ ይልቁኑ አፍሪካውያን ለነጻነታቸው ያደርጉት የነበረውን ትግል ማገዝ በመቻልዋና ለአፍሪካ አንድነት መቋቋም በሰጠችው ድጋፍ ሳቢያ መሆኑን ደጋግመን አይተናል፡፡ይህ ክርክር እስከወዲያኛው የተዘጋ አይደለም በየጊዜው የሚነሳ ብቻ ሳይሆን እንደቀደመው ጊዜ ቀደም ሲል የተዋለ ውለታ እየተጠቀሰ መሻገር ፍጹም አይቻልም፤የጎደለውን ለይቶ ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡ 10ኛው መሪ ፕላን ከተማቱ በ2032 ተመራች ዓለም አቀፍ ከተማ የማድረግ ራዕይ ሰንቋል፡፡ይህን ራዕይ ዕውን ማድረግ የሚያስችሉ ግቦችና ተግባራት በየጥናት ርዕሱ በከተማ ልማት ፕላን መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎች ያጠኗቸውን ፈንጠቂ ትናቶች መሰረት ተለይተው በስልታዊ ፕላኑ ተካትተው ተግባራዊ መሆን ጀምረዋል፡፡ የከተማ ፕላን ጉዳይ ስፓሺያል ጉዳ ብቻ አይደለም፤ ከሰው ልጅ አስተሳሰብ ጋር ቁርኝት ያላቸው ከመሬትና ከገጸ ምድር ጉዳዮች በላ የሆኑ እጅግ ጠናና ጉዳዮችን የሚይዝ ነው፡፡ ፕላኑም ልማቱም ለሰው እንጂ አልተዘጋጀምና የከተማዋን ልማት ከሰው ልጅ ልማት ነጥሎ ማየት ለውድቀት ራስን ማዘጋጀት ነው፡፡ በመሪ ፕላን ዝግት ወቅት ፈንጣቂ ጥነት ካቀረቡ ምሁራን መካከል ዶ/ር ምህረት ደበበና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይህነኑ ጉዳ አጽንኦት ሰጥተውታል፡፡ ቀደም ሲል የተዘጋጁት የከተማይቱ መሪ ፕላኖች ያለመተግበራቸው መንስኤ ሌሎች በርካታ ጉዳች የመኖራቸውን ያክል ሕዝቡ የከተማው ነዋሪ ማለት ነው ነባራዊ እና ህሊናዊ ሁኔታ ባግባቡ ተተንቶኖ የከተማ ፕላንና ልማት ፕላን ዝግጅትና ትግበራ መሠረት ማድረግ አለመቻሉ ነው፡፡ በመሪ ፕላን ዝግጅት ሰር አበርክሮምን የመሳሰሉ አለም ያጨበጨበላቸው ታዋቂ የከተማ ፕላን ባለሙያዎች ለአዲስ አበባ ፕላን አዘጋጅተዋል፡፡ ነገር ፕላኖቹ እንደታለመው ከተማዋን ማዘመን አልቻሉም ህዝቡንም ነዋሪ ማድረግ አልቻሉም ፤ለምን ብሎ መጠየቅ ለመፍትሄው ማንደርደሩ አይቀርምና ቀደም ሲል እንደተገለጸው ከበርካታ ጉዳች አንዱ ምን አልባት ቁልፍ ለሆነው ከተሜነት መፍጠር ትኩረት አለመነፈግ ያሻል፡፡ 2.ነባራዊ ሁኔታ ሀ. ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮች አዲስ አበበ ከተማ ሁሉም የሚኖርባት ናት ድሀው ሀብታሙ መካከለኛ ገቢ ያለውም የሚኖርባት ከተማ ናት፡፡ ምን አልባትም የሀገሪቱ አጠቃላ ማንነት የሚነበበው አዚሁ አዲስ አበባ ከተማ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም ውለኛ ተመልካችም አጠኚም ካለ፡፡ በየትኛውም ዓለም እንዲህ አይነቱ የነዋሪዎች ኢኮኖሚያዊ ስብጥር እንግዳ አይደለም፡፡ ልዩ የሚሆነው ከተሞቹ ጉዳዩን ተቀብለው የሚያስተናግዱበት ሁኔታ ነው፡፡ በከተማቱ ለሚስተዋለው ድሕነት ዋነኛው መንስኤ ስራ አጥነት እንደሆነ የከተማ አስተዳደሩ ሪፖርቶች ያጠይቃሉ፡፡ ስራ አጥ ከሆት ዜጎቻችን መካከል የሚልቁት ወጣቶች ናቸው፡፡ የወጣቶች ስራ አተነት ችግር የመሆኑን ያክል በቴክኒክና ሙያ ስራ ዘርፎች በቀላሉ አሰልጥኖ ስራ መፈጠር ከተማቱንም ሆነ ሀገሪቱን ወደፊት ማራመድ የሚያስችል የሚያስጎመጅ ዕምቅ አቅም ነው፡፡ በዚህ ረገድ የከተማው አመራሮች ትልቁ ፈተና ከአመለካከት ጋር የሚያያዝ ችግር መሆኑ ይገለጻል፡፡ ስለዚህ ዋናው ጉዳይ ከተሜነት ላይ ያለ ችግር ነው ማለት ነው፡፡ (ከተሜነት ዘቅ ብለን እንበይነዋለን፡፡) እንዲህ ዓይነቱ የጨለመ የሚመስል ዐውዳዊ ችግር ቢኖርም የጊዜን ሀብትነት የተረዱ ሳረፍደባቸው የሚሮጡ ትጉሃንም አሉ፡፡ የነዚህን ዘመኑን የዋጀ አመለካከት እርሾ አድርጎ ሌሎች የደነዘዙትን ዞ መውጠት የከተማው አመራር ቁለፍ ስራ ተደርጎ ሊታይ ይገባል፡፡ የከተማዋ ገቢም በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱ ይታወቃል፡፡ እርግጥ ነው ዝቅ ብለን በምናነሳቸው ጉዳች ሳቢያ የውጪ ሀገር ቱሪስቶች ወደ ሀገራችን የሚገቡትም ሆነ የሚወጡት በዲስ አበባ በኩል ነው፤ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ ቆይታቸውን ማራዘም የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ አይደለምና ከዘረፉ መገኘት የሚገባውን ያክል መጠቀም አልተቻለም፡፡